የጠምባሮ ህዝብ የልዩ ወረዳ ጥያቄ በምን መነሻ ነው?

    የጠምባሮ ህዝብ ልዩ ወረዳ የመሆን ጥያቄ
የጠምባሮ ህዝብ የልዩ ወረዳ ጥያቄ በምን መነሻ ነው?
  1. እራስን በራስ ማስተዳደር አለመቻሉ ፦ የሚያገኛቸው ብዙ ማህበራዊ፤ እኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞች ስላሉት፡ይህም ሲባል በባለፉት ስርዓቶች ምንም እንኳን ህዝቡ ይህን ልዩ ወረዳ የራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳይ መሆን ጥያቄ ከ1984 ጀምሮ እየጠየቀ የቆየ ቢሆንም ከላይ ካሉ ከራሱ ሆድ ወዳድ ልጆችና ከዞን መስተዳደር ከሚፈልቀው ማስተባባያ እንዲሁም ከገዛ ልጆቹ በሚደርስበት ጫና ጥያቄው ባለመመለሱ ምክንያት ለዘመናት እየተበደለ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት የራሱን ጉዳይ በራሱ መወሰን አልቻለም። ስለዚህ የህዝቡን ጥያቄ በቅርብ ምላሽ የሚሰጥ ባለመኖሩ ከልማት ተጠቃሚነት ወደኋላ ቀርቷል። መሰረተ ልማት የለም። ጠምባሮን ከሌላ ዞንና አጎራባች ክልሎች ጋር የሚያገናኝ መንገድ ባለመኖሩ ህዝቡ ከሌላው ወገኑ ተቆራርጦ ኖሯል። የገዛ ልጆቹ እንኳን ከላይ ካለው አስተዳደር ጋር ተጣምረው በሙስና ስዘፈቁ እያየ ግን እርምጃ ለመውሰድ ባለመቻሉ የበይ ተመልካች ሆኖ ቆይቷል። በከተማዋ መብራት በወር አንዴ ስመጣ ህዝቡ በደማቅ አንድ የሀገር መሪ/የጦር መኮንን ድል አድርጎ ስመጣ የሚደረግ አይነት አቀባበል እያደረገ ከተማዋ ውስጥ ምንም አይነት ልማት የማይታስብበት ደረጃ ደርሷል። ይህ ብቻ አይደለም ፤አሁንም ዉሃን ከወንዝ እየቀዱ የሚጠጡ የወረዳው 95% ህዝብ ያለበት በኢትዮጵያ ብቸኛው ከተማ ለመሆን በቅቷል።አሁንም በዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን እናቶች በቀኝና ግራ እጃቸው ጀርካን እንደተሸከሙ ፤ በጀርባቸው ጨቅላ፤ጡት ያልጠገበ ልጃቸውን ተሸክመው የሚኖሩበት ብቸኛው የኢትዮጵያ ወረዳ ቢኖር የጠምባሮ ወረዳ ነው። በመሆኑም የህዝቡ ስቃይ ከቀን ወደቀን እየባሰ ወጣቶች ተስፋ በመቁረጥ ባልባሌ ቦታ ከመዋላቸው የተነሳ ለአባላዘር በሽታና ሴቶች ደግሞ ለጾታዊ ትንኮሳ እየተዳረጉ፤አደገኛ እጾች በከተማዋ እየተበራከቱ በሚያስገርም ፍጥነት በማደግ ላይ ናቸው። ክፋት በከተማዋ ባልተለመደ መልኩ እየነገሰ በመምጣቱ አንዱ ሌላለኛውን አጥፍቶ ካልኖረ መኖር አልችልም ብሎ እስከሚያስብ ድረስ ተስፋ መቁረጥ የነገሰበት ወረዳ ሆኗል።ራስን በራስ አለማስተዳደር የራስን እድል ሌላ ሰው/ቡድን እንድወስን እድል አሳልፎ ስለሚሰጥ በዚህም በግልጽ በሚባል ደረጃ ከዞኑ ከሌላው ተነጥሎ ጉዳት ስደርስበት ቆይቷል።
  2. ከከምባታ ህዝብ ጋር ስነጻጸር ለመስተዳድራዊ መዋቅሮች መራቁ ፤ ወረዳው የሚገኘው ከዞኑ በረጅም ኪ.ሜ.ርቀት ስለሆነ የወረዳው ህዝብ ፍትህ በከፍተኛ በከፍተኛ አመራሮቹ ስጓደል ፍትሕ ፍለጋ ወደዞን ፍ/ቤት እየተንከራተተ ቆይቷል። ከዚህም የተነሳ አብዛኛው ተበዳይ ርቀቱን በማሰብ ተስፋ ቆርጦ የፍትሑን ጉዳይ ለአምላኩ በመተው የፍትሕ ጥያቄው ሳይመለስለት ቆይቷል። ይህም ለተደጋጋሚ ጥፋቶችና የፍትሕ መጓደሎች እንድዳረግ አድርጓል። 
  3. የጂኦግራፊያዊ አቀማመጡ ለልማት ተጠቃሚነት ያለው አስተውጽኦው አነስተኛ መሆኑ ፡ ጠምባሮ ወረዳ በደቡብ የሀድያ ዞን በሰሜን ሀደሮና ዶንጋ ልዩ ወረዳ ፤ በምስራቅ ከሾኔ ማዞርያ ፤በምዕራብ ከዳውሮ ዞን ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከነዚህ ከአራቱም አቅጣጫ ሲታይ ያለበት ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ከሌሎቹ ጋር እኩል ተወዳድሮ የሚያመች  ባለመሆኑ እንደእድል እንኳን የመሰረተ ልማት እንዳያገኝ በጂኦግራፍያዊ አቀማመጡ የታደለ በለመሆኑ ልዩ ድጋፍ የሚሻ በመሆኑ ትኩረት ካልተሰጠው ፍትሓዊ የልማት ተጠቃሚነት ልረጋገጥ አይችልም።   
  4. ለዘመናት ስጠይቀው የቆየ ጥያቄው በመሆኑ ፦ ህዝቡ በተዳጋጋሚ የሚያነሳቸውን የልማትና የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ዞኑ መመለስ ባለመቻሉ ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለው ዕምነት ከተሸረሸረ ቆይቷል። በመሆኑም ባዲሱ አስተዳደር የልማት ጥያቄዎች እንዲሁም የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ይፈታሉ ብሎ ስለሚያምን የክልሉ መንግስት አጽንኦት ሰጥቶ እንድያየው ይፈልጋል።
  5. እራሱን ፤ባህሉንና ወጉን በሚገባ ለማስተዋወቅ የራሱ አስተዳደርና በጀት ስለሚያስፈልገው ፦  የጠምባሮ ህዝብ እስካሁን እራሱን በሚገባ ሳያስተዋውቅ በመቆየቱ ምክንያት በተለያዩ ሚዲያዎች ጋዜጠኞች ስሙን እንኳን በትክክል ለመጥራት ስቸገሩ በተደጋጋሚ ብዙ ጊዜ መስማታችን በጆሮችን ጭው የሚል የ"ንቁ" መልዕክት ማስተላለፉ በቂ ማስረጃ ነው።ይህም የሆነው ጠምባሮን እራሱን ለማስተዋወቅ ባለመፈልጉ ሳይሆን በተደጋጋሚ ከላይ ካሉ አስተዳደሮች በቂ ትኩረት እራሱን እንድያሳድግ ባለመሰጠቱ ብቻም ሳይሆን ምቹ ሁኔታዎች ባለመፈጠራቸው ስለሆነ ለአብነትም ያህል ከዱራሜ የዞኑ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የጠምባሮ ስም ተጠርጎ ባዶ ቦታ በማስቀረት የከምባታ ዞን ብቻ እንደሆነ ለማስመሰል ጥረት መደረጉና ይህ እንዲህ እንዳለ ግን የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች አይተው እንዳለዩ ሆነው ማለፍን መምረጣቸው በቂ ማሳያ ነው። በመሆኑም የጠምባሮ የልዩ ወረዳ ጥያቄ የልማት ሳይሆን በዋናነት የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጉዳይ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ ነው።   

Comments

Popular posts from this blog